Job 9

ኢዮብ

1ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2“በርግጥ ነገሩ እንዲህ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤
ነገር ግን ሥጋ ለባሽ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?
3ሰው ከእርሱ ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፣
ከሺሕ ጥያቄ አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።
4ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ ነውና፤
እርሱን ተቃውሞ ያለ አንዳች ጕዳት የሄደ ማን ነው?
5ሳያውቁት፣ ተራሮችን ይነቅላቸዋል፤
በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።
6ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤
ምሰሶዎቿንም ያንቀጠቅጣል።
7ፀሓይን ያዝዛታል፤ አትወጣምም፤
ከዋክብትንም በማኅተም ያሽጋል።
8እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቷል፤
በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል።
9እርሱ የድብና የኦሪዮን፣
የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤
10የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮችን፣
የማይቈጠሩ ታምራትንም ያደርጋል።
11እነሆ፤ በአጠገቤ ሲያልፍ አላየውም፤
በጐኔም ሲሄድ፣ ልገነዘበው አልችልም።
12ቢነጥቅ፣ ማን ይከለክለዋል?
‘ምን መሥራትህ ነው?’ የሚለውስ፣ ማን ነው?
13 እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤
ረዓብን የሚረዱ እንኳ ይሰግዱለታል።

14“ታዲያ፣ ከእርሱ ጋር እሟገት ዘንድ፣
ልከራከረውም ቃላት እመርጥ ዘንድ፣ እንዴት እችላለሁ?
15ጻድቅ ብሆንም እንኳ፣ ልመልስለት አልችልም፤
ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ላደርግ የምችለው የለም።
16ጠርቼው ‘አቤት!’ ቢለኝም፣
ያዳምጠኛል ብዬ አላምንም።
17በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፤
ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል፤
18ምሬትን አጠገበኝ እንጂ፣
ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም።
19የኀይል ነገር ከተነሣ፣ እርሱ ኀያል ነው!
የፍትሕም ነገር ከተነሣ፣ መጥሪያ ሊሰጠው
ሰብዓ ሊቃናት ይመልከቱ፤ የዕብራይስጡ ሊሰጠኝ ይላል።
የሚችል ማን ነው?
20ንጹሕ ብሆን እንኳ፣ አንደበቴ ይፈርድብኛል፤
እንከን የለሽ እንኳ ብሆን፣ በደለኛ ያደርገኛል።

21“ያለ ነቀፋ ብሆንም እንኳ፣
ስለ ራሴ ግድ የለኝም፤
የገዛ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።
22ሁሉም አንድ ነው፤
‘እርሱ ጻድቁንና ኀጥኡን ያጠፋል’ የምለውም ለዚህ ነው።
23መዓት ወርዶ ድንገት ሰው ሲጨርስ፣
በንጹሓን መከራ ይሣለቃል።
24ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣
እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤
ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል?

25“ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤
አንዳችም ደስታ ሳያይ ያልፋል።
26ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ፣
ለመንጠቅ ቍልቍል እንደሚበርር ንስር ይፈጥናል።
27‘ማጕረምረሜን እረሳለሁ፤
ገጽታዬን ቀይሬ ፈገግ እላለሁ’ ብል፣
28ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣
መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።
29በደለኛ መሆኔ ካልቀረ፣
ለምን በከንቱ እለፋለሁ?
30ሰውነቴን በሳሙና
ወይም በረዶ
ብታጠብ፣
እጄንም በልዩ መታጠቢያ ባነጻ፣
31ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣
በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።

32“መልስ እሰጠው ዘንድ፣ እሟገተውም ዘንድ፣
እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።
33በሁለታችን ላይ እጅ የሚጭን፣
በመካከላችንም የሚዳኝ ቢኖር፣
34ግርማው እንዳያስፈራኝ፣
እግዚአብሔር በትሩን ከእኔ ላይ ቢያነሣ፣
35ሳልፈራው በተናገርሁት ነበር፤
አሁን ባለሁበት ሁኔታ ግን፣ አልችልም።
Copyright information for AmhNASV